ጣናን እንታደግ!

Let us Save Lake Tana!!!
 

Let us read it, it will give us a clue about the cause of the existing problem of lake Tana

(Note: this view is a personal observation of the writer) 

Let us see the root causes of the existing problem of Lake Tana in four aspects:

  1. External loading of nutrients from the watershed of Tana Basin through the major rivers that feed Lake Tana.
  2. Domestic and industrial wastes: sewage discharged from towns/cities located along the periphery of the lake discharged into the waterways that flow to the lake or directly into the Lake.
  3. The disturbance of the natural/environmental flow of waters that flow into and/or discharged from Lake Tana has an impact on the self-purification capacity/ waste assimilation capacity of the Lake and sediment deposition.

      We can see this from three perspectives:

  • The reservoirs which have been built in the upstream rivers that feed Lake Tana have the advantage to decrease sediment flow into the lake, but they have an impact on the rate and volume of flow of water that flows into the lake.
  • The water discharged from Lake Tana with the Abay outlet is controlled in" the Chara Chara Weir". The closing of some of these gates to reserve more water for Tana Belese hydropower may disturb the natural flow of water. This, in turn, has an impact on the waste assimilation capacity of the lake.
  • The withdraw of water for the operation of "Belese hydropower" may consume more water that disturbed the natural flow of water and result in a reduction of self- purification capacity of lake Tana. It also brought sediment deposition on the lake since it forced to flow in an unnatural way.
  1. Expansion of recession agriculture and deforestation in the basin (Lack of delineated buffer     zone)

Solutions:

I have given the solutions in accordance with the above-listed factors: -  

  1. Practice scientific and integrated sustainable agricultural activity in the watershed of Tana basin.
  • Reduction of external loading of nutrients. In case the use of fertilizer by the surrounding farmers is mandatory, it is better to use less phosphate content fertilizers since phosphate is the limiting reactant for the growth of algal bloom.
  • Devising alternative strategies like livelihood diversification of rural households that reside in the basin of Lake Tana. Gradually changing the livelihood of rural households from crop production to animal production, planting timber trees and/or long-lasting fruits like mango and Avocado. This will help the reduction of nutrients on permanent basis at the same time diversify the livelihoods of the households. This will be a permanent solution for the reduction of nutrients that comes from the basin.
  1. Let us see the solutions for factor two in two aspects:
  • Hotels, industries, and residents located around Tana basin and especially in periphery of the lake have to stop discharging their domestic as well as industrial wastes and sewage into the waterways that inflow into Lake Tana or directly into the lake.
  • Constructing a buffer zone that is free from the intervention of human beings and animals. The constructing buffer zone serves as a natural wetland to filtrate the polluted water that carries nutrients.

3. Let us see the solutions for factor three in two aspects:

  • As much as possible it is better to maintain the environmental/natural flow of water that inflow into and discharged from the Lake. This includes the water withdrawal for Tana Belse hydropower from the lake and the water discharged in the Abay outlet from the Lake. These need a commitment from the Government. For example, the Government has to look for an alternative source of hydropower energy other than Tana Beles in the long run. Like the Grand Renaissance Dam. 
  • The regional government should appeal for the Federal government "the polluter pays principle". And spent the compensation which is gained from the Federal government to the expenses to save Lake Tana from its current situation.  
  1. The government has to discourage and inhibit the expansion of recession agriculture and deforestation in the basin. Instead, it has to encourage afforestation on a larger scale.

Though the above solutions are thought to be helpful to get rid of the stated problem in a permanent way, it is obvious that the solutions suggested will take long time to be fully implemented. Hence, at the present time, to recover the lake from the invasive water hyacinth, we have to internalize the problem, unite the community, and utilize the available simple machines and manpower to prevent the lake from this dangerous species.  

        

                                 Dr. Hailu Sheferaw
     Department of Chemistry, College of Natural Science, Bahir Dar University

ጣናን ከተጋረጠበት ችግር እንታደግ!

ለጣና ችግር መነሻ ይሆናችሁ ዘንድ ጊዜ ሰጥታቸሁ አንብቡት!!!

ማስታወሻ፡- ይህ ጽሁፍ የጸሃፊው የግል ምልከታ ነው

የጣናን ችግር መንስዔዎች በሶስት መንገድ መመልከት ይቻላል

  1. በጣና ተፋሰስ ዙሪያ ከሚገኙ እርሻ ማሳዎች የሚነሳው ጎርፍ፤ አፈር ፣ ደለል እና ማዳበሪያ (በንጥረ ነገር የበለጸገ) ውሃ ተሸክሞ በተለይም በዋና ዋናዎቹ የጣና ገባር ወንዞች አማካኝነት የሚገባው ወደ ጣና ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የባህር ሸሽ እርሻ እና የደን መራቆትም የራሳቸው የጎላ ተጽእኖ አላቸው።
  2. በጣና ተፋሰስ ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች በተለይም በሀይቁ ዳር ከሚገኙት አካባቢዎች የሚፈሰው ቆሻሻ ፍሳሽ እና ፅዳጅ ወደ ጣና በሚፈሱት ወንዞች አማካኝነት እና እንዲሁም  በቀጥታ ወደ ጣና የሚገባ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ
  3. ወደ ጣና በገባር ወንዞች አማካኝነት የሚፈሰው እና ከጣና የሚወጣው የውሃ መጠን ተፈጥሯዊ የፍሰት ይዘት መዛባት በጣና ተፈጥሯዊ እራስን የማከም አቅም ላይ ተጽእኖ ማሳደር ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ይህን በሶስት መንገድ መመልከት ይቻላል፡፡
  • የመጀመሪያው፡- ምንም እንኳን ለመስኖ ስራ ታስበው በላይኛው ተፋሰስ በወንዞች ላይ የሚሰሩ ግድቦች ደለል ወደ ሃይቁ እንዳይገባ የማስቀረት አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም ወደ ሃይቁ የሚገባውን ተፈጥሯዊ የፍሰት መጠን ይቀንሳሉ፡፡
  • ሁለተኛው፡- ሃይቁ ብዙ ውሃ እንዲያከማች በሚፈለግበት ወቅት በዓባይ ወንዝ መውጫ ላይ በተሰራው የጨረጨራ  የፍሰት መጠን መቆጣጠሪያ የሚደረገው የውሃ ፍሰት መጠን ቁጥጥር፤ በሃይቁ ተፈጥሯዊ ራሱን የማከም አቅም ላይ ተጽእኖ ያለው በመሆኑ
  • ሶስተኛው፡- ለጣና በለስ ሃይድሮ ፓወር ማመንጫ ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ከሃይቁ የሚወሰደው ውሃ፤ የሃይቁን ራሱን በራሱ የማከም አቅም መቀነስና የደለል ክምችትን በሃይቁ ላይ የሚፈጥር በመሆኑ፡፡

መፍትሄዎች
ከላይ ለተጠቀሱትእያንዳንዱ ችግር መፍትሄ የሚሆኑ ጉዳዮችን በሁለት መንገድ ማየት ይቻላል፡-

  1. በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሰውን ችግር በተመለከተ፡- በዋናነት ሳይንሳዊ የተቀናጀ የግብርና ዘዴ በተፋሰሱ መተግበር ሲሆን ይህንንም በሁለት መንገድ መመልከት ይቻላል፡፡
  • በተቻለ መጠን ከተፋሰሱ ወደ ጣና አፈር፣ ደለል እና ማዳበሪያ በገባር ወንዞች አማካኝነት እንዳይገባ መከላከል፡፡ ይህን ለማድረግ በተፋሰሱ በሚደረግ የሰብል ማምረት ሂደት አርሶ አደሮች ዝቅተኛ የፎስፈረስ ንጥረ ነገር ያለው የማዳበሪያ አይነት እንዲጠቀሙ ማድረግ፣ በተፋሰሱ የደን ሽፋንን መጨመርና አርሶአደሮች የአግድም እርሻና የእርከን ስራ በማሳቸው ላይ እንዲተገብሩ ማድረግ እና በዘለቄታ የባህር ሸሽ እርሻን ማስቆም፡፡
  • በተፋሰሱ የሚገኙ አርሶአደሮችን የአኗኗር ዘዴ ቀስ በቀስ ከሰብል ማምረት ወደ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ መቀየር፡፡ ይህም ሲባል ንብ ማነብ፣ የእንስሳት እርባታ እንዲሁም ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ዓይነቶችን በመጨመር ከሰብል ምርት ጥገኝነት በማላቀቅ ወደ ሃይቁ የሚገባውን የማዳበሪያ መጠን በዘላቂነት መቀነስ ያስችላል፡፡
  1. በተራ ቁጥር ሁለት የተመለከተውን ችግር በተመለከተ
  • ቆሻሻ ፍሳሻቸው እና ፅዳጃቸውን በቀጥታ ወደ ጣና ወይም ወደ ጣና ወደሚፈሱ ገባር ወንዞች የሚለቁ ግለሰቦች፣ ሆቴሎችም ሆኑ ሌሎች ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ፡፡
  • የሀይቁን ዙሪያ የሚከልል ከሰውም ሆነ ከእንሰሳ ንክኪ ነፃ የሆነ ወሰን መስራት፡፡ በተሰራው ወሰን ውስጥ ቆሻሻ ተሸክመው የሚገቡ ወንዞችን በተወሰነ መልኩ ሊያጣራ የሚችል እንደ ሳርና መሰል እጽዋቶችን መትከል፡፡
  1. በተራ ቁጥር ሶስት የተጠቀሰውን ቸግር በተመለከተ፡-
  • በተቻለ መጠን ወደ ጣና የሚፈሱ ወንዞችም ሆነ ከጣና የሚወጣውን ውሃ የፍሰት ይዘቱን እንዲጠብቅ ማድረግ፡፡ ለዚህም የመንግስትን ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡ይህም ማለት መንግስት ዘለቄታ ባለው መንገድ የሃይድሮ ፓወር ኢነርጅ ምንጩን ከጣና በለስ አውጥቶ ወደ ሌሎች አማራጮች ማዞርን ይጠይቃል፡፡ ለምሳሌ ወደ ፊት ከሚጠናቀቀው የህዳሴ ግድብ፡፡
  • የፌደራል መንግስቱ በጣና አማካኝነት ለሚያገኘው ጥቅም፤ በተጠቀመው ልክ ማካካሻ እንዲከፍል የክልሉ መንግስት መጠየቅና የሚገኘውን ማካካሻ ሐይቁ ለተጋረጠበት ችግር መፍትሄ ማዋል፡፡

ሆኖም ግን ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች በዘላቂነት ችግሩን ለመቅረፍ የሚረዱ ቢሆኑም ረጅም ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ስአት ሃይቁ የተጋረጠበትን የእንቦጭ አረም ችግር በፍጥነት መፍታት የሚቻለው ችግሩን ወደ እራሳችን አድርገን ባለን የሰው ሀይል እና ባሉን ማሽኖች ነገ ዛሬ ሳንል በመረባረብ ልንከላከል ይገባል፡፡

   ዶ/ር ሀይሉ ሽፈራው

ከኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ሳይንስ ኮሌጅ