በቆለላ ሶላር መንደር የተቀናጀ ልማት የመስክ ምልከታ
ከፍተኛ አመራሩ በቆለላ ሶላር መንደር የማህበረሰብ አገልግሎት ሳይት የተቀናጀ ልማት የመስክ ምልከታ አካሄደ
በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ የተመራው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ ቆለላ ሶላር መንደር በዩኒቨርስቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የተከናወኑ የተቀናጀ ልማት ተግባራትን ጎበኘ፡፡
የተከናወኑ ተግባራትም በዋናነት በግብርናው ዘርፍ በታዳሽ በኃይል አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማትና በትምህርት ዘርፍ የአቅም ግንባታ ናቸው፡፡